ቦሌ ወረዳ 14 አስተዳደር
Bole Sub City Woreda 14 Administration
ይህ ይፋዊ የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 አስተዳደር ዌብሳይት ነው።ሁሉንም ትኩስ መረጃዎች በአንድ ቦታ ባሉበት እናደርሳለን።ፈቅዳችሁ አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን።
መረጃ እንመግባለን
ድማማ ድል ማፅናትና ማብዛት
ማስተዳደር ሰላምን ነው
የመልካም ምኞት መግለጫ
ከሁሉ አስቀድሜ ኢትዮጵያዊያን ለዘመናት እንዳንጠቀምበት የተደረገው የአባይ ጉዳይ በታሪክ እጥፋት በብልፅግና ትውልድ ፣ በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በሳል አመራር ሰጪነት ታላቁ የህዳሴ ግድብ ተጠናቆ በአዲስ ዘመን መባቻ በመመረቁ የተሰማኝን የማያባራ ልባዊ ደስታ እየገለጽኩ በወረዳችን ከኢላላ እስከ ድማማ የዋንጫ ቃል ኪዳን ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ የመጣልን አዲስ አመት በኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን ላይ በመሆኑ የምንቀበለው በታላቅ ደስታ ፣ በታላቅ ተስፋ እና በብልጽግና መንፈስ ነው ፡፡
የወረዳ አስተዳደሩን በመወከል የአዲስ አመት የመልካም ምኞት መግለጫ መልእክቴን ሳስተላልፍ ከፍ ያለ ክብርና ኩራት እየተሰማኝ ነው ፡፡
