በሀሳብ የበላይነት የሚያምን ትዉልድ መገንባት የምንግዜም ስራችን መሆን አለበት

በሀሳብ የበላይነት የሚያምን ትዉልድ መገንባት የምንግዜም ስራችን መሆን አለበት::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ የበጀት ዓመቱን የ 3 ወራት እቅድ አፈፃፀም እና የቅንጅታዊ አሰራር ስራዎችን ገምግሟል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አአቶ በትግሉ ኪታባ እንደተናገሩት ሃሳብ መሸጥ፤የሀሳብ የበላይነትን መያዝ እና በሀሳብ የበላይነት የሚያምን ትዉልድ መገንባት የምንግዜም ስራችን መሆን አለበት በማለት ፤በበጀት ዓመቱ ጠንካራ ጎኖችን ይበልጥ በማስቀጠል ክፍተቶችን ፈጥኖ በማረም በቀጣይ የላቀ ዉጤት የምናስመዘግብበት ጊዜ እንዲሆን ሁላችንም መትጋት አለብን ብለዋል።

ምክትል ቢሮ ሃላፊው አክለውም በዘርፉ የተፈጠሩ ምቹ ሁኔታዎችን በመጠቀም ከማዕከል እስከ ወረዳ እንዲሁም ከሌሎች ተቋማት ጋር ተቋማዊ እና ቅንጅታዊ አሰራርን ይበልጥ ማጠናከር የተደራጀና ዘመናዊ አሰራርን መከተል፣የሚዲያ ፕላት-ፎርሞችን ማስፋትና ተከታዮችን ማብዛት ይገባል ነው ያሉት፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘዉዱ ከበደ በበኩላቸዉ በክረምት ወራት በከተማዋ በተከናወኑ ከተማ አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የተለያዩ ህዝባዊ ንቅናቄዎች፣በተለያዩ የልማት ስራዎች፣በበጎ ፈቃድ ተግባራት እና መንግስት ባስመረቃቸዉ ትላልቅ እና ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ከአመራር ጀምሮ በተደራጀና በተናበበ ቅንጅታዊ አግባብ ትኩረት አድርጎ የማስፈፀሚያ ዕቅድ ከማዘጋጀት ጀምሮ አጀንዳዎችን እና መልዕክቶችን በመቅረፅ፤ መረጃዎችን በመሸጥና ለህዝብ በማስረፅ ሀገራዊ የጋራ መግባባት በመፍጠር ረገድ ቢሮዉ የሚጠበቅበትን ሚና በላቀ ሁኔታ በመፈፀም ኃላፊነቱን መወጣት መቻሉን ተናግረዋል።

በ2018 ይህን የላቀ ትጋትና አፈፃፀም የበለጠ ለማስቀጠልና ዉስንነቶች ለማረም ከማዕከል እስከ ወረዳ ያለዉ የኮሙኒኬሽን መዋቅር በተደራጀ አግባብ በሙሉ አቅም ወደ ስራ መግባቱን አስታዉሰዉ በዚህ በጀት ዓመት ድርብ ድርብርብ ተልዕኮ ያለብን በመሆኑ ከመቸዉም ጊዜ በተሻለ ተግቶ በመስራት እና በሁለንተናዊ መልኩ የበለጠ ነጥረን በመዉጣት በኮሙኒኬሽን አግባብ ስራዎቻችንን በመሸጥ ከተማችንን ብሎም ሀገራችንን ወደ ላቀ ከፍታ ለማሻገር የሚመጥን ስራ መስራት ከእኛ ይጠበቃል በማለት መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።

በበጀት ዓመቱ 1ኛ ሩብ ዓመት ከማዕከል እስከ ወረዳ ባሉ መዋቅሮች የዝግጅት ምዕራፉ ተግባር ጨምሮ የዉስጥና የዉጪ ተቋማዊ እና ቅንጅታዊ አሰራርን ይበልጥ በማጠናከርና በማዘመን የከተማዋን ሁለተናዊ እንቅስቃሴዎች በአጀንዳ እና በመልዕክት፤በተደራጀና በተናበበ መንገድ በመምራት እና የህዝቡን የመረጃ ፍላጎት በማርካት ዉጤታማ ስራዎች መሰራታቸዉን በቀረቡት ሪፖርቶች ተመላክቷል፡፡