fb img 1763032514398

ተምሳሌታዊቷ ከተማችን በተለወጠ አስተሳሰብ ፣ ቃልን በተግባር በመተርጎም የዳበረ የስራ ባህል በሁሉን አቀፍ የከፍታ ጉዞ ላይ ትገኛለች።

ተምሳሌታዊቷ ከተማችን በተለወጠ አስተሳሰብ ፣ ቃልን በተግባር በመተርጎም የዳበረ የስራ ባህል በሁሉን አቀፍ የከፍታ ጉዞ ላይ ትገኛለች።

ፅኑ የሆነ ህዝባዊ መሰረት ፣ ቁርጠኛ የሆነ የአመራር ትጋት እንዲሁም የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ያለው
የከተማችን ፈጣን ዕድገት እና አስተማማኝ ሰላም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በመቀናጀት እና በመናበብ ፣ ህዝባችን በማስተባበር የሚከናወኑ የሰላምና የፀጥታ ስራዎቻችንም የከተማችንን አስተማማኝ ሰላም ከማረጋገጣቸው ባሻገር በህዝባችን መካከል ወንድማማችነት ፣ እህትማማችነት እንዲሁም አብሮነት እንዲጎለብት ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ነው፡፡fb img 1763032524270

የህዝባችንን አዳጊ ፍላጎት ለማሟላት እንዲሁም የኑሮ ደረጃውን ለማሻሻል ቀን እና ሌት የሚሰራባት አዲስ አበባ ታላላቅ ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ሁነቶችን በስኬትና በድምቀት በማስተናገድ የስዕበት ማዕከልነቷን አጠናክራለች።

በየደረጃው የሚደረጉ ስራን መሰረት ያደረጉ ግምገማዎች ፣ ክትትልና ድጋፎችም በተመዘገቡ ስኬቶች የነበሩ ጥንካሬዎች እንዲቀጥሉ ፣ ክፍተቶች ደግሞ ፈጥነው እንዲታረሙ ትልቅ አቅም ፈጥረዋል።

በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲ እና የሰላምና ፀጥታ አመራሮች እየተከናወኑ የሚገኙ ቅንጅታዊ ስራዎችን የገመገሙ ሲሆን የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችንም የጋራ አድርገዋል።fb img 1763032516310

የከተማችንን አስተማማኝ ሰላም ዘላቂ ለማድረግ አመራሩም አባላትም የአስተሳሳብ እና የተግባር አንድነታቸውን በማጠናከር ግንባር ቀደም ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆን ህዝባችንም የማይተካ ሚናውን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተመላክቷል።

ወቅታዊና ነባራዊ ሁኔታዎችን ቀድሞ በመረዳት ጥልቅ የሆኑ የአዝማሚያ ትንተናዎችን ማድረግን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተጠቁሟል።fb img 1763032532902

የአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የተጀማመሩ አበረታች ጥረቶችን ለማጠናከር ፣ ብልሹ አሰራሮችን እና ሌብነትን ለማስወገድ የፓርቲያችንን መዋቅሮች እንዲሁም የአባላትን አቅም በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባም በአፅንዖት ተገልጿል::

በውይይቱ ላይ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፣ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ም/ ኃላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አለምፀሀይ ሽፈራው እና ሌሎችም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ተገኝተዋል።