photo 4 2025 11 09 20 17 14

“የዘመናት የነዋሪዎቻችን ጥያቄዎች ለመመለስ እንተጋለን”

የወረዳው ነዋሪዎች ለዘመናት ሲጠይቋቸው የቆዪ የመሰረተ ልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በአጭር ጊዜ ለመመለስ እየተሰራ ነው።

በቦሌ ክ/ከተማ የወረዳ 14 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ማንደፍሮ ተመስገን የተመራ ልዑካን ቡድን የወረዳው ነዋሪዎች በተለያዩ ጊዜያት ሲያነሷቸው የቆዩ የመሰረተ ልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት የመስክ ምልከታ አድርገዋል።

photo 4 2025 11 09 20 17 14

በክላስተር ሁለት አዋሰብ ግሪን ኤሪያ የልማት ጥያቄ እንዲሁም ክላስተር አራት ከወረዳ 13 ጋር የሚያዋስነው ርዝመቱ 1.5ኪሎ ሜትር መንገድ የወንዝ ዳርቻ የድጋፍ ግንብ ባለመኖሩ ዝናብ በሚጥልበት ወቅት የውሃ ሙላት ነዋሪዎች ሲቸገሩ ኑረዋል።

በተጨማሪም መንገዱ የኮብል ንጣፍ አለመኖሩ ለእግረኛ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ መሆኑና ተሽከርካሪ የማይገባበት በመሆኑ ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር ሆኖ ዘመናትን ተሻግሯል።

photo 3 2025 11 09 20 17 14

የአስተዳደሩ አመራሮች በዛሬ ጉብኝታቸው የነዋሪዎች ጥያቄ ተገቢነት ያለው በመሆኑ በአጭር ጊዜ ለመፍታት እየተሰራ ሲሆን የዛሬው ምልከታም የዚሁ አካል ነው።

ጥቅምት 16/18ዓ.ም

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *