“ድማማ ልምድ ይሰጣል ፤ ልምድ ይቀበላል”
የየካ ክ/ከተማ አስተዳደር በቦሌ ወረዳ 14 አስተዳደር የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ አደረገ።
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደርና የወረዳ አመራሮች በቦሌ ወረዳ 14 አስተዳደር በድል የተጠናቀቀውን የኢላላ ልምድና ተሞክሮ ለማስፋት በአሁኑ ድማማ መንደር በመገኘት የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ አድርገዋል።

በልምድ ልውውጡ የየካ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ኃይሌና የየካ ወረዳዎች ዋና ስራ አስፈፃሚዎችና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ማንደፍሮ ተመስገን ፣ የወረዳ 14 ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወገኔ ተሻገር እና የወረዳው ጠቅላላ አመራር በተገኘበት የካዎችን ተቀብለው የስኬት ልምድና ተሞክሯቸውን አካፍለዋል።
መስከረም 26/18ዓ.ም
Yeshaw, [09/11/2025 10:25 PM]



