የወረዳው ብሎኮች እየተሰራ ባለው ስራ ከጨለማ ወደ ብርሃን እየተቀየሩ ነው።
የቦሌ ክ/ከተማ አመራሮች በወረዳ 14 አስተዳደር እየተሰሩ ያሉ ሞዴል ብሎኮችን እየጎበኙ ነው።
በወረዳው የተመረጡ አምስት ብሎኮችን ሞዴል ለማድረግ እየተሰራ ባለው ስራ ባለፉት ስምንት ቀናት የተሰሩ ስራዎችን በዚህ ምሽት የክ/ከተማው አመራሮች እየጎበኙ ነው።

“የተቀናጀ ሞዴል ብሎክ ልማት ለቦሌ ወረዳ 14 ማንሰራራት” በሚል መሪሃሳብ ብሎኮችን ሞዴል ለማድረግ የተጀመረው ስራ ዛሬ ስምንተኛ ቀን ላይ ሲደርስ ብሎኮች ከጨለማ ወደ ብርሃን እየተቀየሩ በአስደናቂ ሁኔታ ወደ ሞዴልነት እየተቀየሩ ነው።
የክ/ከተማው አመራሮች በጉብኝታቸው ወረዳው የተመረጡ ብሎኮችን ሞዴል ለማድረግ እየሰራ ያለው ስራ ብሎኮችን ከጨለማ ወደ ብርሃን የቀየረበት ሁኔታ አስደማሚ መሆኑን በመግለፅ የተሰራው ስራ ለሌሎችም ተምሳሌት እንደሆነም ተናግረዋል።
ጥቅምት 27/18ዓ.ም



