photo 5 2025 11 09 22 20 42

“አስተዳደሩ ለኢላላ ስኬቶች እውቅና የሰጠበት እና ለድማማ ቀጣይ ምዕራፍ የተዘጋጀበት የምስጋናና እውቅና መርሃግብር አካሄደ”

“አስተዳደሩ ለኢላላ ስኬቶች እውቅና የሰጠበት እና ለድማማ ቀጣይ ምዕራፍ የተዘጋጀበት የምስጋናና እውቅና መርሃግብር አካሄደ”

የወረዳው አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት የላቀ ስኬት ሲያስመዘግብ ከፍተኛ ሚና ለነበራቸው ተቋማትና ባለሙያዎች እውቅና ሰጥቷል።

የእውቅናና ምስጋና መርሃ ግብሩ የተካሄደው የቦሌ ክ/ከተማ ፐብሊክና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዋሲሁን አለማየሁ ፣ የወረደ 14 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሱራፌል ባያብል ፣ የወረዳ 14 ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወገኔ ተሻገር ፣ የወረዳው አስተባባሪና አጠቃላይ አመራሮች ፣ አባገዳዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ፣ ባለሙያዎች ፣ የፌዴራል ፓሊስና አዲስአበባ ፖሊስ ተወካዮች ፣ የሰላም ሰራዊት አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት ነው።

photo 3 2025 11 09 22 20 42

በቦሌ ክ/ከተማ የወረዳ 14 አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት የላቀ ስኬት በማስመዝገብ ከአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር እውቅናና ሽልማት ሲያገኝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ለነበራቸው ተቋማት ፣ ባለሙያዎችና ግለሰቦች ዛሬ እውቅናና ሽልማት ሰጥቷል።

አስተዳደሩ በ2017 በጀት አመት በኢላላ የዋንጫ ቃልኪዳን በርካታ ስኬቶችን በማስመዝገብ ከ11ዱ የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳዎች 3ኛ ደረጃ በመውጣት የዘመናዊ ተሽከርካሪ መኪና ከከተማ አስተዳደሩ መሸለሙ የሚታወቅ ሲሆን ለዚህ ድል በየደረጃው አሻራቸውን ያሳረፉ ጽ/ቤቶች ፣ ባለሙያዎችና ግለሰቦች ዛሬ በደማቅ ስነስርዓት በተካሄደው የአስተዳደሩ የምስጋናና እውቅና መርሃግብር ላይ ተመስግነዋል ፣ እውቅናና ልዩ ልዩ ሽልማትም ተበርክቶላቸዋል።

photo 10 2025 11 09 22 20 42

የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሱራፌል ባያብል ሁላችሁም የድርሻችሁንና የምትችሉትን ሁሉ በማድረግ ለዚህ ስኬት ስለደረስን በአስተዳደሩ ስም አመሰግናለሁ በማለት በ2017 በጀት አመት የተመዘገቡ ስኬቶችን በ2018 በጀት አመት ማፅናትና ማብዛት እንደሚገባ በመግለፅ በኢላላ የዋንጫ ቃልኪዳን የነበረው የጽ/ቤቶችና ባለሙያዎች ጤናማ የስራ ፉክክርና ትብብር መቀጠል አለበት ብለዋል።
ጥንካሬዎቻችን ግለታቸውን ጠብቀው ማስቀጠል ብሎም የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በጊዜ የለኝም መንፈስ ፈጥኖ ማረም የነገ ሳይሆን የአሁን ተግባር መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል።

የቦሌ ክ/ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዋሲሁን አለማየሁ የዘንድሮው የወረዳ 14 አስተዳደር ስኬት ለሌሎችም ተሞክሮ የሚሆን ነው።ይቻላል ብላችሁ ከምንም በመጀመር እንደሚቻል በላቀ ድል አሳይታችኋል ፤ በኢላላ ትልቅ አሻራ አሳርፋችኋል ።የቀጣዩ ድማማ ከዚህ እንደሚልቅ ይጠበቃል በማለት የነበሩ ጥንካሬዎችን ማስቀጠል ውስንነቶችን ማረም የዛሬ ተግባር መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።

ዝግጅቱ በ2017 በጀት አመት በኢላላ የዋንጫ ቃልኪዳን የተመዘገቡ ስኬቶችን በሚዘክር በሂደቱ የተስተዋሉ ክፍተቶችን በሚያርም እና በቀጣይ የድማማ ዋንጫ ቃልኪዳን የታቀዱ ተግባራትን በድል ለመፈፀም የሚያስችልና ለበለጠ ስራ የሚያተጋ ፣ የሚያነሳሳና የሚያዘጋጅ እንዲሆን ታቅዶ የተዘጋጀ የምስጋናና እውቅና መርሃግብር ነው።

በመጨረሻም የ2018 በጀት አመት የድማማ ዋንጫ ቃልኪዳን ስምምነት በአመራሮችና ባለሙያዎች መካከል ከተፈረመ በኋላ
በ2017 በጀት አመት በከተማ ፣ በክ/ከተማና በወረዳ የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ለወጡ ጽ/ቤቶች ፣ የቡድን አስተባባሪዎች ፣ ባለሙያዎችና ለተለያዩ ተቋማት እውቅና በመስጠት ፤ የዋንጫና ሰርትፍኬት ሽልማት በማበርከት መርሃግብሩ ተቋጭቷል።

ጳጉሜን 3/17ዓ.ም