በቦሌ ክ/ከተማ የወረዳ 14 ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፓለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ በብልጽግና ፓርቲ አሰራር እና አደረጃጀት መመሪያዎች ዙርያ ለወጣት ክንፍና ጥቃቅን አባላት ስልጠና ሰጥቷል።
በስልጠና መድረኩ የወረዳ 14 ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታምራት ጅፋር የፓርቲውን አሰራር ፣አደረጃጀትና መመሪያ አውቆ ተፈፃሚ እንዲሆንና ፓርቲው የሚፈልገውን ቁመናና ቁርጠኝነት እንዲወጡ ለማስቻል አባላቱ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የተደራጀ ስልጠና ስለሚያስፈልግ ይህ መድረክ እንደተዘጋጀ ገልጸው ስልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ እና የተሰጠውን ስልጠና በመተግበር አባላት የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ምክትልና የፖለቲካ የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ልጃለም ደመቀ የብልጽግና ፓርቲ አሰራርና አደረጃጀት መመሪያዎች በትክክል መረዳት ለተልዕኮ ስኬታማነት ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸዋል ።
ሰልጣኞቹም የወሰዱትን ስልጠና ወደ ተግባር ለመቀየር ዝግጁ እንደሆኑና በየጊዜው የሚሻሻሉ እና የሚወርዱ አሰራሮች በጉባኤ የሚጸድቁ መመሪያዎች ለሁሉም አባላት እንደዚህ ተደራሽ መሆኑ አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል።
ለፓርቲው አባላት የሚሰጡ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጠል ሲሆን ነገ እሁድ ለመኖሪያ አባላት ስልጠና እንደሚሰጥ መረጃውን ከስልጠና መርሃግብሩ ላይ ተመልክተናል።
ጥቅምት 22/18 ዓ.ም



